image
image
image
image
image

በንፋስ ስልክ ላፍቶ የትራንስፖርት አገልግሎት ጥራትንና የአሽከርካሪዎችን ሥነ-ምግባር ለማሻሻል ውይይት ተካሄደ"

ጥቅምት 26/02/19, 2018
በንፋስ ስልክ ላፍቶ የትራንስፖርት አገልግሎት ጥራትንና የአሽከርካሪዎችን ሥነ-ምግባር ለማሻሻል ውይይት ተካሄደ" የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአሽከርካሪዎችን ግንዛቤ ለማሳደግና የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። የመድረኩ ዋና ዓላማ የአሽከርካሪዎችን የሥራ ሥነ-ምግባር ማሳደግ፣ የትራፊክ ሕጎች እንዲከበሩ ማድረግና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በጋራ በመለየት ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጥ ነው። በምክክር መድረኩ መክፈቻ ላይ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ውቢት ድንቃ እንደገለጹት፤ አሽከርካሪዎች በከተማዋ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ ለማሻሻል መሰል ውይይቶች ወሳኝ ናቸው ብለዋል። በመድረኩም የአሽከርካሪዎች ሥነ-ምግባር፣ የተገልጋይ አያያዝ እና በዘርፉ ያሉ ተደራሽነትና ቅልጥፍና ችግሮችን በጋራ መፍታት ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት ተካሂዷል። በተጨማሪም ተሳታፊዎች የትራንስፖርት ሥርዓቱን ለማሻሻል የሚያስችሉ አስተያየቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ አሽከርካሪዎች በበኩላቸው ሥራቸውን በኃላፊነት ስሜት ለመምራት፣ የስምሪት ቁጥጥርን ለማሳለጥና የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች