image
image
image
image
image

‹‹በሩብ ዓመቱ የታዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስኬታማነትን ማስቀጠል ይገባል፡፡›› አቶ ያብባል አዲስ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ

ጥቅምት 10, 2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከአመራርና ባለሙያዎች ጋር በገመገሙበት ወቅት እንደተገለፀው የከተማዋን የትራንስፖርት ሂደት ተደራሽ፣ አስተማማኝ፣ ምቹ፤ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ከባቢያዊ ተስማሚነቱ የተረጋገጠ ለማድረግ በርካታ ተግባራት እተከናወኑ እንደሚገኙ ተገልፅዋል፡፡ የቢሮ ሃላፊ አቶ ያብባል አዲስ እንተናገሩት በሩብ ዓመቱ ከታዩ ስኬታማ ስራዎች መካከል የበጎ አድራጎት እና ኢኒሼቲቭ ስራዎች ፣የአደረጃጀትና አሰራር ተግባራት፣የመመሪያ እና ደንብ ዝግጅቶች፣የፍላጎት እና አቅርቦት የማመጣጠን የተጀመሩ ስራዎች፣የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ተግባራት፣የተካሄዱ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣አሮጌ ተሸከርካሪዎችን በአዲስ ለመተካት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ስራዎችን በማስቀጠል እና ተግባራትን በላቀ ሁኔታ በመፈፀም በሁለተኛው ሩብ ኣመት ዋንኛ የዕቅድ መተግበሪያ ጊዜ ማድረግ እንደሚገባ አሳታውቀዋል፡፡ የቢሮ የፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዋሲሁን ታረቀኝ በበኩላቸው የታየውን የተሻለ የዝግጅት ምዕራፍ ከግምት በማስገባት በቀጣይነት ከመረጃ አያያዝ ፣ከሪፎርም ስራዎች፣ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ከሰው ሃይል ስምሪት፣ከበጀት አጠቃቀም እና ፋይናንስ፣ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት አንፃር ትኩረት በማድረግ በተሻለ መልኩ መፈፀም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች