image
image
image
image
image

የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ በመገኘት ልምድ ልውውጥ አደረጉ!

ታህሳስ 27, 2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በትራንስፖርት አገልግሎት ዘርፍ "አመሰጋኝ ማህበረሰብ ለመፍጠር" እየተካሄደ ባለው የስራ እንቅስቃሴ በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ በመገኘት ልምድ ልውውጥ አደረጉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራአስኪያጅ አቶ ሱራፌል ባያብል የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለመጡ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ሲያስተላልፉ በተቋሙ ላይ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመልካም ተግባር በሰከነ መንገድ መፍታት፣ የተሰጠው አመራር፣ የባለሙያዎች ታታሪነትና ተነሳሽነት እና ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩ እንደ እንደ ቢሮ እውቅና የተሰጠው ተግባር መሆኑ ጠቅሶ ወደ ሌሎች ቅርንጫፎች ብወሰድ የተሻለ ተግባር መሆኑ ገልጿል። በልምድ ልውውጡ የቢሮ አደራጃትና ሪፎርም፣ መረጃ አያያዝ፣ ምቹ የስራ አከባቢ/Ergonomics፣ የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሳለጥ የተሰሩ የቴክኖሎጁ ስራዎችን ሌሎች ለቅርንጫፎች የራሳቸውን ፈጠራ በመጨምር እንደተሞክሮ ማስፋት እንዳለበቸው ተገልጿል። የቂርቆስ እና ልደታ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት እንደገለፁት ያገኙትን ልምድ በቀጣይ የዕቅዳቸው አካል አድርገው እንደሚተገብሩት በመግለፅ ትልቅ ልምድና አቅም ያገኘንበት መድረክ ነው ሲሉ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች