image
image
image
image
image

ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ፡፡

ጥቅምት 4, 2018
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስራ አስኪያጆች እና ከማዕከል ዳይሬክተሮች ጋር በመሆን በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሶስት ወራት በዕቅድ የያዛቸውን እና ያከናወናቸውን ተግባራት ገምግሟል፡፡ በበጀት ዓመቱ ሶስት ወራት ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም፤ የአገልግሎት አሰጣጥ፤ የመልካም አስተዳደር እና የሀብት አጠቃቀም በማጎልበት ፣የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን በማስተዳደር፣የህዝብ እና ጭነት ትራንስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት በማሳደግ፣የስትራቴጅክ ጥናት እና የዘርፉን የቴክኖሎጂ አቅም በማጠናከር ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አስታውቋል፡፡ የሪፎርም ስራ ላይ ትኩረት ተሠጥቶ መሰራታቸው፣ከተቋማትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራዎች መጠናከራቸው፣የህዝብ ትራንስፖርት አቅርቦትና አገልግሎት መሻሻላቸው፣የብዙሃን ትራንስፖርት ማጓጓዝ ድርሻ ዕቅድ መሳካታቸው፣የክትትልና ድጋፍ ስርዓታችን መሻሻላቸው፣የኮሚኒኬሽን ስራዎቻችን የዘርፉን ሥራዎችና እንቅስቃሴዎች ያጎላ መሆኑ፤የተለያዩ የክረምት በጎ አድራጎት፣የእንሼቲቭ ሥራዎችንና የ90 ቀን ዕቅድ በአግባቡ ውጤታማ በሆኑ መልኩ ማከናወናቸው በጥንካሬ ተነስተዋል፡፡ በቀጣይነትም የሪፎርም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ስራዎችን በስታንዳርድ መሰረት እንዲከናወኑ ማድረግ፤የምሽት ትራንስፖርት አገልግሎትን ማሳደግ፤የህዝብ ትራንስፖርት የስምሪት ስርዓትን የማሻሻል ስራ ላይ የተለየ ትኩረት ማድረግ፡፡በሌብነትና ክራይ ሰብሳቢነት ላይ ትኩረት በማድረግ እርምጃ የመውሰድ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም በግምገማው ወቅት ተጠቅሷል፡፡

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች