Welcome to Nifas Silk Lafto Transport Branch Office!       እንኳን ወደ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሰላም መጡ!       Baga gara Waajjira Damee Geejjibaa Nifaas Silk Laaftootti dhuftan!!

የቅ/ጽ/ቤቱ ሥራ አስኪያጅ መልእክት

በ2018 በጀት ዓመት በቅ/ጽ/ቤታችን የቁልፍና አብይ ተግባራትን ለማስፈፀም በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረው የአገልግሎት አሠጣጡ ከሌላ የስራ ሂደት ጋር በአንድ ታጭቆ የነበረበት ሁኔታ በመኖሩ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ያልነበረ በመሆኑ ሠፊ ችግሮችን እያጋጠሙን ቆይተዋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ባለስልጣን ፈርሶ በቢሮ ስር ከተዋቀረ በኋላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በመልሶ የማደራጀት ስራ በመስራት የፈጻሚዉን ተግባር እና ኃላፊነት በሚገባ እንዲያዉቅ ግንዛቤ በመስጠት የውጭ እና የውስጥ አገልግሎቶችን ውጤታማነትና ቀልጣፋነት ለማረጋገጥ የሚያዳግቱ የተለያዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ እንዲያስችል ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት የከተማ ትራንስፖርት አቅም በማሳደግ በስምሪትና በቁጥጥር ሚዛናዊ እንዲሆን ለማድረግና የህዝብ ትራንስፖርት ችግር ለመፍታት አቅም በፈቀደ ሁኔታ ተግባሩ በበቂ የሠው ኃይል በማሟላትና ተጨማሪ የድጋፍ ሠጪ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ በማድረግ ያሉትን መደበኛ ታክሲዎች ጨምሮ አገልግሎቱን የተሻለ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ እንዲሁም የነዳጅ ጭማሪን ተከተሎ የታሪፍ ማሻሻያ ቢደረግም ህብረተሰቡን እያማረረ ያለዉን ከታሪፍ በላይ የማስከፈል፤ መስመር የመቆራረጥ ፤መስመር ያለመሸፈን፤ የታሪፍ ዝርዝር ያለማንጠልጠል ፤ያለታፔላ መንቀሳቀስ የመሳሰሉትን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በጅምር ደረጃ ለውጥ ማምጣት የተቻለ ሲሆን በቀጣይ ዘርፉ ከሚሠጠው አገልግሎት አኳያ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንና በተለይም በዘርፉ የሚስተዋሉ የብልይሹ አሰራር አስተሳሰብና ተግባር ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ አገልግሎቱ ፈጣን ቀልጣፋና የህዝቡን ፍላጎት እርካታ ያረጋገጠ አገልግሎት ለመስጠት እንተጋለን፡፡

አቶ ሱራፌል ባያብል , የንፋስ ስልክ ላፍቶ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሥራ አስኪያጅ
image description